
የሲብክመ ፍትህ ቢሮ ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ።
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም
የሲብክመ ፍትህ ቢሮ ተጠሪ ተቋም የሆነው የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም በዛሬው ዕለት ተገምግሟል።
በበጀት ዓመቱ በተጠሪ ተቋማት የሕግ ማስከበር፣ የሕግ በላይነትን የማረጋገጥ፣ የዜጎችን መብት መጠበቅና ማስጠበቅ፣ የተቋሙ ሪፎርም ስራዎች እንዲሁም የዜጎች መታረምና መታነጽ ጋር የተከናወኑ ስራዎችን በማስመልከት የተቋሙ ስራዎች ተገምግሟል።
የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ባለፉት 3 ወራት ውስጥ በርካታ ተግባራት ስለማከናወኑ በቀረበው ሪፖርት ተገምግሟል፡፡ በቀጣይ ስራዎች በዋናነት በተቋሙ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የተቋሙ ስራዎችን በቴክኖሎጂ ማስደገፍና ማቀላጠፍ እንዲሁም በቋሙ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማጠናከር የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ የክልሉ የማረሚያ ተቋም የምርትና የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል።
በመድረኩን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ማሩ የመሩ ሲሆን የቢሮው የማኔጅመንት አባላት፣ የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተው የሩብ ዓመት አፈጻጸም ተግምግሟል፡፡
ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!!
ለበለጠ መረጃ
አድራሻችን
ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL